በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንሶን በተመለከተ የተጠናቀረ ዘገባ


ፋይል- ኮንሶ
ፋይል- ኮንሶ

የኮንሶ ነዋሪዎች ከ80 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው የኮሚቴው አባል ነኝ ያሉ አቶ ገመቹ ጎንፋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።

በኮንሶ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እንደማይሰጡ፣ጤና ጣቢያዎችም ጭምር መዘጋታቸውን ለደሃ ደሃ የሚሰጠው የምግብ ዋስትና መቋረጡን ጭምር ይገልፃሉ።

የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በዞን እንጠቃለል ለሚለው ጥያቄ ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን ገልፀው። መንግስት መስሪያ ቤቶችን አልዘጋም፤ ጥያቄያችን ተቀባይነት ከሌለው አንሰራም ብለው የቀሩት ሰራተኞቹ ናቸው ይላሉ።

በጉዳዩ ላይ የሕገ-መንግስት ባለሙያ በማነጋገር የተጠናከረ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኮንሶን በተመለከተ የተጠናቀረ ዘገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:40:55 0:00


XS
SM
MD
LG