በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኮንሶ ሰው ወዴት እንደሚያመለክት ግራ ገብቶታል” አቶ ገመቹ ገንፌ ከኮሚቴው አባላት አንዱ


A 17th lava fissure erupts hundreds of feet in the air during a volcano outbreak in Pahoa, Hawaii.
A 17th lava fissure erupts hundreds of feet in the air during a volcano outbreak in Pahoa, Hawaii.

ኮንሶ ወረዳ መኾኑ ቀርቶ ዞን እንዲኾን ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት ባሕላዊ አባታቸውን (የኮንሶ ንጉስ) ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች እንደታሠሩባቸው ከኮሚቴው አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንፌ ገለጹ፡፡ጽዮን ግርማ አቶ ገመቹ ገንፌን አነጋግራቸዋልች፡፡

ሕገ መንግሥስቱ በሚፈቅደው መሠረት ከ55 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላት ወኪለነት ኮንሶ ወረዳ መኾኑ ቀርቶ ዞን እንዲኾን ጥያቄ ቢያቀርቡም የባህል አባታቸውን (የኮንሶ ንጉስ) ጨመሮ ወደ 200 ሰው መታሠሩን እንዲሁም ከተማው በውጥረት ውስጥ መኾኑን ከኮሚቴው አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንፌ ገልጸዋል፡፡

አቶ ገመቹ ጎንፋ
አቶ ገመቹ ጎንፋ

አቶ ገመቹ “የኮንሶ ሕዝብ ከልዩ ወረዳነት ዞን ሊኾን እንደሚገባ ሕዝቡ ምክንያቱን ጠቅሶ እየተጠቀ ባለበት ወቅት ይባስ ተብሎ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ትተዳድርበት ከነበረው ልዩ ወረዳነት ካለሕዝቡ ፍላጎት ወደ ወረዳነት ዝቅ ተደረገች ይህም አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰን ሕገመንግስቱ በሚያዘው መሠረት ከ55 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበን ከተማዋ በዞን እንድተዳደር ጠየቅን ነገር ግን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ፋንታ የባህል አባታችንን ጨምሮ ወደ 200 ሰዎች ታሥረውብናል›› ይላሉ፡፡

ጽዮን ግርማ አቶ ገመቹ ገንፌን አነጋግራቸዋልቸ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“የኮንሶ ሰው ወዴት እንደሚያመለክት ግራ ገብቶታል” አቶ ገመቹ ገንፌ ከኮሚቴው አባላት አንዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለማግኘት \የወረዳው ኃላፊዎችና የደቡብ ክልል ባለሥልጣናት በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ የአብዛኞቹ ስልክ ባለመመለሱ ምክኒያት ምላሻቸውን ማካተት ሳንችል ቀርተናል፡፡

የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]
የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]

XS
SM
MD
LG