በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ልጄ የልጆች አባት አርሶ አደር ነበር"የሟች አባት አቶ አዛዥ አሬሮ


የሟች ሞሌ አዛዥና የሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ሥርዓት(ከኮሚቴው አባላት የተላከ ፎቶ)
የሟች ሞሌ አዛዥና የሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ሥርዓት(ከኮሚቴው አባላት የተላከ ፎቶ)

እሁድ ዕለት በኮንሶ ደበና በተባለች መንደር ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን የሟች ሞሌ አዛዥ አባትና የሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ አጎት ተናግረዋል።ወደ 55 ሺሕ የሚኾኑ ነዋሪዎች ተፈራርመው ኮንሶ ከወረዳ ወደ ዞን ከፍ እንዲል ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት፤ ጥያቄውን ለመንግሥስት ካቀረቡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ መታሠራቸውን ሌሎች ደግሞ በስጋት ተሸሽገው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ጽዮን ግርማ የሟች ቤተሰቦችንና የኮሚቴውን አባላት አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡

በኮንሶ የሚገኙ ወደ 55 ሺሕ የሚጠጉ ነዋሪዎች ተፈራርመው ኮንሶ ከወረዳ ወደ ዞን ከፍ እንዲል ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት፣ጥያቄውን ለመንግሥት ካቀረቡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ መታሠራቸውን ሌሎች ደግሞ በስጋት ተሸሽገው እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው የኮሚቴ አባላት ተናግረዋል፡፡

ይህንንም ተከተሎ በመንግሥት ታጣቂዎች ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደኾነና እሁድ ዕለት ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገለጸዋል፡፡ የሟች ሞሌ አዛዥ አባት አቶ አዛዥ አሬሮ በአስተርጓሚ አማካኝነት ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ በማያውቁት ምክንያት ልጃቸው መገደሉን ይህንኑም ሕዝብና መንግሥት እንዲፈርዳቸው ለመናገር የስልክ ኔትወርክ የሚያገኙበት ድረስ በእግራቸው ተጉዘው እንደመጡ ተናግረዋል፡፡"ልጄ የልጆች አባት አርሶ አደር ነበር"ይላሉ፡፡

ሌላው ሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ ሲኾን ስለሁኔታው ያስረዱት ደግሞ አጎቱ አቶ ኮንበሬ ኮንተሼ ናቸው፡፡ የወንድማቸው ልጂ አርሶ አደርና በድንጋይ ፈለጣ ሥራ ይተዳደር እንደነበር ይናገራሉ። በወቅቱ በቦታው እንዳልነበሩ ጩኸት ሰምተው ሲሄዱ በርካታ ሰው ተሰብስቦ ማየታቸውንና የወንድማቸው ልጅ በጥይት ተመቶ መሞቱን ማረጋገጣቸውን ይናገራሉ።

በኮንሶ ለተቃውሞ ዋና መነሻ ከወረዳ ወደ ዞን ከፍ እንዲል የቀረበው ጥያቄ መኾኑን ይህን ጥያቄ ለመንግሥት እንድናቀርብ ተወክለናል ያሉ የኮሚቴ አባላት ይናገራሉ፡፡የዚህ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ዐሥራ ሁለት ሲኾን አንዱ በእሥር ላይ እንደኾኑ ይገልፃሉ ሌሎች ደግሞ የእስር ስጋት ስላለብን ያለነው አስቸጋሪ በኾነ ቦታ ተደበቀን ነው ይላሉ።

ጽዮን ግርማ ሁሉንም አነጋግራ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

"ልጄ የልጆች አባት አርሶ አደር ነበር" የሟች አባት አቶ አዛዥ አሬሮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ፍሰሃ ጋረደው ጋር ደውለን ስልካቸው ባለመነሳቱ ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ ነገር ግን ይህንኑ አካባቢ በተመለከተ ከአምስት ቀናት በፊት ጠይቀናቸው የተነሳው ጥያቄ በሰላም መመለሱንና ከተማውም ሰላም እንደኾነ ገለፀው ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG