በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታላቁ የኅዳሴ ግድብ Great Reninssance

የዐዲስ አበባው የሕዳሴ ግድብ ድርድር ያለስምምነት ተጠናቋል

የዐዲስ አበባው የሕዳሴ ግድብ ድርድር ያለስምምነት ተጠናቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00

በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ፣ በዐዲስ አበባ የተደረገው ውይይት ያለስምምነት ለመጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ አንዳቸው ሌላቸውን ወቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በድርድሩ የሚሳተፈው “የግብጽ ወገን፣ የ2015ቱን የመርሖዎች ስምምነት የማፍረስ አቋሙን ገፍቶበታል፤” ብሏል።

የግብጽ የመስኖ እና የውኃ ሚኒስቴር ደግሞ፣ ኢትዮጵያ፣ “ምንም ዐይነት ስምምነትን ትቃወማለች፤” ሲል ወቅሷል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹክሪ፣ ለቪኦኤ በሰጡት አስተያየት፣ ለድርድሩ መጓተት ኢትዮጵያ የምትከተለውን መንገድ ተጠያቂ አድርገዋል።

በሌላ በኩል፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ፣ ድርድሩ ውጤታማ ያልኾነው በግብጽ ምክንያት እንደኾነ ገልጸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ግብጽ የሕዳሴው ግድቡን አራተኛ ሙሌት “ሕገ ወጥ” ስትል አወገዘች

ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ

ኢትዮጵያ፣ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን አራተኛ ሙሌት እንዳጠናቀቀች ስታስታውቅ፣ ግብጽ በበኩሏ፣ “ሕገ ወጥ ነው” ስትል አወገዘች፡፡

ሚኒስቴሩ፣ ትላንት እሑድ፣ ጳጉሜን 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ዐዲስ አበባ፣ የግድቡን ሙሌት ለማጠናቀቅ የወሰደችው “የተናጠል” ውሳኔ፣ “እ.ኤ.አ በ2021 ዓ.ም ተቋርጦ ባለፈው ወር ዳግም የተጀመረውን የሦስትዮሽ ድርድር ወደ ጎን የተወ ነው፤” ማለቱን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ “በውስጥ ፈተና፣ በውጭ ጫና ነበረብን። ከፈጣሪ ጋራ የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚኽ ደርሰናል፤” ሲሉ፣ የሕዳሴ ግድቡ አራተኛ ሙሌት እንደተጠናቀቀ፣ ትላንት እሑድ፣ በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በካርቱም በሦስቱ ሀገራት የተፈረመው የ2015 የመርሖዎች ስምምነት፣ ሦስቱ ሀገራት፥ በሕዳሴ ግድቡ ሙሌት እና የመተዳደሪያ ደንቦች ላይ መስማማት እንዳለባቸው የደነገገውን አስታውሷል፡፡

አያይዞም፣ “የኢትዮጵያ የአንድ ወገን አካሔድ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገጉ የተፋሰሱን የታችኛው ሀገራት መብት እና ጥቅም፣ እንዲሁም የውኃ ደኅንነታቸውን ወደ ጎን የተወ ነው፤” ሲልም ተችቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከግብጽ በኩል ስለቀረበው ወቀሳ እስከ አሁን በይፋ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

ኾኖም፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ(ዶር.)፣ ባለፉት አራት ዓመታት፣ የውኃ ሙሌት ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ የዝናም መጠን እንደተገኘና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራትም ላይ ምንም ዐይነት ጉዳት በማያደርስ መልኩ እንደተከናወነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የግድቡ የውኃ ሙሌት፣ ከግንባታው ሒደት ጋራ ጎን ለጎን እንደሚከናወን የምትገልጸው ኢትዮጵያ፣ ይህም፣ ሦስቱ ሀገራት በተፈራረሙት የመርሖዎች ስምምነት መሠረት እንደሚፈጸም በተደጋጋሚ አስታውቃለች፡፡

በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት የሚካሔደው የሦስትዮሽ ድርድር፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2021 ከተቋረጠ በኋላ፣ በነሐሴ ወር በካይሮ አስተናጋጅነት የተካሔደው ውይይትም፣ ተጨባጭ ውጤት እንዳላመጣ ግብጽ ይፋ አድርጋለች፡፡ ለዚኽም “ግትር አቋም ይዛለች፤” ያለቻትን ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡

ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ግብጽ ወቀሳ እና ትችት ጥያቄ የተነሣላቸው፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ ውድቅ አድርገውታል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በግድቡ ጉዳይ ሦስቱንም ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ እንደኾነች የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ በካይሮው ውይይት ላይ፣ “ግብጽስ ከቀድሞው የተለየ ምን አቋም አራምዳለች?” በሚል መጠየቅ እንዳለባት አመልክተዋል፡፡

በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት ጉዳይ፣ ቀጣይ ዙር የሦስትዮሽ ውይይት፣ በዐዲስ አበባ እንደሚካሔድ ይጠበቃል፡፡

ሀመር በኅዳሴ ጉዳይ አውሮፓ ናቸው

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር በዚህ ሳምንት ወደ ስቶክሆልም እና ብራስልስ ተጉዘው በኅዳሴ ግድብ እና እንዲሁም ኢትዮጵያ እና ሱዳን ውስጥ እየተካሄዱ ባሉት ግጭቶች ዙሪያ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የስቶክሆልሙ ዓለም አቀፍ የውሃ ጉዳይ ተቋም በሚያስተናግደው የዓለም የውሃ ሳምንት ጉባዔ ላይ የሚካፈሉት አምባሳደር ማይክ የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም እና ምርምር ተቋም በሚያስተናግደው ውይይት ላይም እንደሚካፈሉ ተመልክቷል፡፡

ሀመር የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዋናው የዩናይትድ ስቴትስ መልዕክተኛ እንደመሆናቸው የውሃ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ተደራሽነትነት የሚመለከቱ ሥምምነቶች ለአፍሪካ ቀንድ ጸጥታ እና መረጋጋት ሊያበረክቱ ስለሚችሉት አስተዋጻኦ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ወደብረሰልስ በማቅናት ኢትዮጵያን እና ሱዳንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

አምባሳደር ሀመር በኢትዮጵያ ጉዳይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በውይይት ለመፍታት ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሕብረት እንዴት ሊደግፉ እንደሚችሉ፤ በተጨማሪም ለሰላማዊ ዜጎች በሚደረግ ጥበቃ አስፈላጊነት ዙሪያም እንደሚወያዩ ተገልጧል።

ልዩ መልዕክተኛው ከአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ሚያደርጓቸው ውይይቶች የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማስቆም ምክኒያት የሆነው ሥምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እና በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሰላም፣ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚሰጡት ድጋፍ ዙሪያም ይመክራሉ ተብሏል።

አምባሳደር ሀመር በሱዳኑ ግጭት የአፈሙዞች ላንቃ እንዲዘጋ፤ ተጠያቂነትን ለማስከበር እና ዲሞክራሲያዊ የሲቪል አስተዳደር ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ የተያዙ አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጥረቶች ዙሪያም ይወያያሉ። ለክልሉ የሚሰጠውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማጠናከር የተያዘው ሥራ ማቀላጠፉ እንደሚቀጥልም መግለጫው ጠቅሷል።

የሕዳሴ ግድብ ውይይት በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሪዎቹ አስታወቁ

የሕዳሴ ግድብ ውይይት በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሪዎቹ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:24 0:00

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስምምነትን፣ በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሠሩ፣ የኢትዮጵያ እና የግብፅ መሪዎች እንዳስታወቁ ሮይተርስ ዘግቧል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ፣ ይህ የሮይተርስ ዜና ከመሰማቱ አስቀድሞ በሰጡን አስተያየት፣ “ድርድሩ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል” አመልክተዋል፡፡

የውኃ ሙሌቱ፣ ከግድቡ የግንባታ ሒደት ጋራ በተጣጣመ መልኩ እንደሚከናወን የገለጹት ፕር. ይልማ፣ የክረምቱ መራዘም፣ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ እና ከፍታው መጨመሩ፣ በሚያዘውና በሚለቀቀው የውኃ መጠን ላይ ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታሕ አል-ሲሲ፣ ካይሮ ላይ ተገናኝተው፣ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ስላለው የሕዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚኖረውን የአጠቃቀም ደንብ በተመለከተ፣ ሱዳንን ጨምሮ በሦስቱ አገሮች መካከል ሲደረግ የነበረውንና የተቋረጠውን ድርድር በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።

የሮይተርስ ዜና ወኪል፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የወጣውን የጋራ መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሁለቱ መሪዎች፣ ስምምነቱን በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተስማማተዋል፤ ተብሏል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታሕ አል-ሲሲ፣ ትላንት ረቡዕ፣ ካይሮ ላይ ተገናኝተው፣ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ስላለው የሕዳሴ ግድብ፣ እንዲሁም በሱዳን በተፈጠረው ቀውስ ላይ እንደተነጋገሩ፣ የግብጹ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

አል-ሲሲ፣ ዐቢይ አሕመድን በቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።ሁለቱ መሪዎች ካይሮ ላይ የተገናኙት፣ በአል-ሲሲ አስተናጋጅነት፣ ስድስት የሱዳን ጎረቤት ሀገራት፣ ለ12 ሳምንታት የዘለቀውን የሱዳን ግጭት አስመልክቶ ለመነጋገር፣ ካይሮ ላይ ካደረጉት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ይፋ ሆነ

የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ይፋ ሆነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:33 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG