በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአባይና የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው


የአባይና የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00

በአባይ አጠቃቀምና በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ጉዳይ የኢትዮጵያ አቋም “ግትርነት የበዛበት” እንደሆነ በመግለፅ የግብፅ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር፣ አምባሳደር ሞሃመድ ሂጋዚ ወቅሰዋል።

“ኢትዮጵያ በግሏ የተናጠል እርምጃ እየወሰደች ነው” ሲሉ ከስሰው “በዓለምአቀፍ ውኃዎች ጉዳዮች ላይ የተናጠል እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም” ብለዋል።

“የቀድሞው የትረምፕ አስተዳደር በሦስቱም አካላት ሊፈረም የተቃረበ ሥምምነት በተሳካ ሁኔታ ማድረስ በቻለበት ጊዜ ዕቅዱ በዋይት ሃውስ በሚካሄድ ሥነ ሥርዓት ለመፈረም ታስቦ ነበር። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ስምምነታቸውን አስቀምጠው ነበር። ያንን የመሰለ ታላቅ ጥረት በኢትዮጵያ መንግሥት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሁላችንም አዝነናል።” ብለዋል አምባሳደር ሂጋዚ ሰሞኑን ሰጥተውት በነበረ መግለጫ።

በሌላ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል የሚኖረው ድርድር ውጤት “የውኃ መጠን ክፍፍልን የሚያመለክትና አስገዳጅነት ያለው ሊሆን እንደማይችል” በኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳዮች የቀድሞ ባለሥልጣንና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“በውኃ ሃብት ላይ የተናጠል እርምጃን የከለከለ ዓለም አቀፍ ሥምምነትም ሆነ ሕግ የለም” ብለዋል አቶ ፈቅአህመድ።

XS
SM
MD
LG