በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀጥታ ም/ቤቱን ፕሬዚዳንታዊ መግለጫ እንደማትቀበለው ኢትዮጵያ አስታወቀች


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ አስገዳጅ ስምምነት ላይ እንዲደረስ የጸጥታው ምክር ቤት ያወጣውን ፕሬዚደንታዊ መግለጫ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል አስታወቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚደንት መግለጫ በአብዛኛው ከኢትዮጵያ አቋም ጋር የሚጣጣም ቢሆንም አስገዳጅ ስምምነት የሚባል ነገር ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ገልጸዋል፡፡

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት በነበረው ስብሰባ ላይ፣ የወቅቱ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የሚደረገውን ድርድር ዳግም እንዲጀምሩ እና በሁሉም ወገን ተቀባይነት ያለው አስገዳጅ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የፀጥታ ም/ቤቱን ፕሬዚዳንታዊ መግለጫ እንደማትቀበለው ኢትዮጵያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00


XS
SM
MD
LG