በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኅዳሴ፣ በሱዳን አቢዬይ፣ በሳዑዲ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ


ፎቶ ፋይል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ፎቶ ፋይል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

መንግሥት የመከላከያ ሰራዊቱን ከትግራይ ክልል ያስወጣበት ዋነኛው ምክንያት ኢትዮጵያ ለተጋረጡባት የውጭ ስጋቶች ጦሩን ለማዘጋጀት መሆኑን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በተለይ ከሕዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሱዳን ጥያቄ መሰረት፣ ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪዎች ከአቢዬይ ግዛት መውጣት ካለባቸው ተገቢውን ዕውቅና እና ክብር አግኝተው መሆን እንዳለበት ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግሥታት መግለጿንም ተናግረዋል፡፡

በአራት ቀናት ብቻ ከሳዑዲ ከ9ሺህ 900 በላይ ዜጎች መመለሳቸውን ጠቅሰው፣ ይህም በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኅዳሴ፣ በሱዳን አቢዬይ፣ በሳዑዲ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00


XS
SM
MD
LG