ዋሺንግተን ዲሲ —
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዲያስፖራው ከ1 ቢሊዮን 260 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ባለፉት አስር አመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዲያስፖራው 1 ቢሊዮን 263 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤትን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ ዘግቧል፡፡
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አስር ዓመታት መቆጠሩን ዘገባው አመልክቶ እስካሁን ከከውጭና ከአገር ውስጥ እስከ ነሃሴ 30 ቀን 2013 15 ቢሊዮን 931 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መዋጣቱን አስታውቋል፡፡
የግድቡ ሁለት ተርባዮኖች በቅርብ ወራት ውስጥ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማመንጨት እንደሚጀምሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡