በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታላቁ ኅዳሴ ግድብ 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሊጀምር ነው


ፎቶ ፋይል፦ ታላቁ የኅዳሴ ግድብ
ፎቶ ፋይል፦ ታላቁ የኅዳሴ ግድብ

ኢትዮጵያ እአአ 2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድቧ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር አስታወቀች።

ይህም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅሟን በ14 ከመቶ እንደሚያሳድግላት ዛሬ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን መናገራቸውን ከናይሮቢ ሮይተርስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ በድረ ገጽ በይነ መረብ በተካሄደ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ፌስቲቫል ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፣

"ኢትዮጵያ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጄክቶች ትልቁ በሆነው በታላቁ ኅዳሴ ግድቧ እአአ ከሚቀጥለው 2022 ጀምራ 700 ሜጋ ዋት ማመንጨት ትጀምራለች" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG