በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በኅዳሴው ግድብ ጉዳይ ሁሉንም የሚያግባባ አቋም ላይ እንደምትሠራ አልጄሪያ ቃል ገብታልናለች" አምባሳደር ዲና ሙፍቲ


አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የአረብ ሊግ ቀጣይ ሊቀመንበር ትሆናለች ተብላ የምትጠበቀው አልጄሪያ፤ ሊጉ በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ሁሉንም ወገን የሚያግባባ አቋም እንዲይዝ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ መግለጿን ኢትዮጵያ አስታወቀች።

39ኛው የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከነዚህም አንዱ የአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ የአረብ ሊግ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ሁሉንም ወገን የሚያግባባ አቋም እንዲይዝ ሀገራቸው እንደምትሠራ ቃል መግባታቸውን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከቱርክ የጦር መሳሪያዎችን ሸምታለች በሚል ግብጽ ጉዳዩ እንደሚያሰጋት መግጿን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በሰጡት ምላሽ፣ "ኢትዮጵያ ነጻ ሀገር እንደመሆኗ ከማንም ጋር ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት የመፍጠር መብት አላት" ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡


XS
SM
MD
LG