No media source currently available
ግድቡ ሞልቶ ውሀው በአናቱ ላይ ሲፈስ በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱት የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ ሁለተኛው ሙሌት መጠናቀቁ በሁለት ተርባይኖች ኃይል ለማመንጨት እንደሚያስችል ተናግረዋል። የክረምቱ ዝናብ ከፍተኛ መሆኑ ግድቡ በፍጥነት እንዲሞላ ማስቻሉንም የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ከዚህ በኋላ እስከ ሦስት ወራት ባሉት ጊዜያት የሚኖረው ቀጣይ ሥራ ኃይል ማመንጨት መሆኑን ተናግረዋል፡፡