ለአየር ንብረት እየተለወጠና ለምድራችን እየጋለች መምጣት ዋናው ምክንያት የሰው ልጅ ተግባር ነው ሲሉ የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪዎች የሚያሰሙትን ድምዳሜ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥርጣሬ ነው የሚያዩት፡፡
ሪፖብሊካውያን ብዙሃን የሆኑበት የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያቀረቧቸውን ዕጩ ሹመት አፅድቀዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ከዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት “የመውጣት ስትራቴጂ” ባለው እርምጃ እየገፋ ነው።
የዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን አንድ ሣምንት ሆነው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ውስጥ የሚዘረጉ የከርሰ-ምድር ዘይት ማስተላለፊያ ቦዮችና ቱቦዎች ግንባታ ሥራዎች እንዲጀመሩ ትናንት (ጥር 17/2009 ዓ.ም.) የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ ፈርመዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ውድድር ወቅት በገቡት ቃል መሠረት ሕጋዊ ሠነድ የሌላቸው መጤዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስና በሜክሲኮ መካከል ግንብ በመስራቱ ጉዳይ ላይ እየገፉ ነው፡፡
ከጥር 14 / 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በጋሞ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ታስረው የነበሩ 13 አመራሮቹና አባላቱ ትናንት ምሽት ላይ መፈታታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አስታውቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን አትላንቲክ ሀገሮች የጦር ትብብር ድርጅት (ኔቶ) “ጊዜ ያለፈበት” ነው ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው የአውሮፓ መሪዎችን አስደምሟል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለካቢኔአቸው ካቀረቧቸው ዕጩ ባለሥልጣናት የአገረ ገዥ ኒኪ ሄሊን፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርነት ሹመት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ትናንት አፅድቋል፡፡
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ፣ አስረዳደሩ ለመገናኛ ብዙሃን ለመዋሸት በጭራሽ ዓላማ የለውም ብለዋል፡፡
በዚህ ሳምንት በኦፊሴል ስራ የጀመሩት የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጡ ነው፤ አስቀድመው በምረጡኝ ዘመቻቸው የሰጧቸው አስተያየቶችም ለተለያዩ ቡድኖች ስጋትና ተስፋ ሆነዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ካቢኔ ዕጩዎች እየፈተሹ ባዶ ቦታዎችን በዚህም ሳምንት ውስጥ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአሜሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ባለ ተስፋ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ አሜሪካ ውስጥ የሚፈጠር መከፋፈል ግን የሀገሪቱ መለያ የሆኑ እሴቶችን ያጠፋሉ በማለት ስጋታቸውን ገለፁ። ኦባማ በመጨረሻው የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ትናንት ረቡዕ በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ፣ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላደረጉት ውይይትም አንስተዋል።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዋይት ሃውስን ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ አስረክበው ይሰናበታሉ።
ከበርቴው ነጋዴ ዶናልድ ትራምፕ ነገ፤ ዓርብ ጥር 12/2009 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ደጅ ላይ ቃለ-መሃላ ሲፈፅሙ የሃገራቸው 45ኛ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ።
በዩናይትድ ስቴትስ የጆርጂያው ተወካይ ጆን ሉዊስ ከነገ በስቲያ ዓርብ በሚካሄደው የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ላይ እንደማይገኙ ያላቸውን ዕቅድ ተከትሎ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሲቪል መብቶች ታጋዩ ላይ የትችት ናዳ አውርደዋል።
ከነገ በስቲያ ዓርብ፣ ዶናልድ ትራምፕ ቃለ-መሃላ ፈፅመው 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ አሜሪካ ለውጭ ሀገሮች የምትሰጣቸው አንዳንድ ድጋፎች ከዚያ በኋላ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል እየተሰማ ነው፡፡