No media source currently available
በአሜሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ባለ ተስፋ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ አሜሪካ ውስጥ የሚፈጠር መከፋፈል ግን የሀገሪቱ መለያ የሆኑ እሴቶችን ያጠፋሉ በማለት ስጋታቸውን ገለፁ። ኦባማ በመጨረሻው የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ትናንት ረቡዕ በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ፣ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላደረጉት ውይይትም አንስተዋል።