በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴኔቱ ከትራምፕ ዕጩዎች የአራቱን አፀደቀ


ኒኪ ሄሊ (አምባሳደር)
ኒኪ ሄሊ (አምባሳደር)

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለካቢኔአቸው ካቀረቧቸው ዕጩ ባለሥልጣናት የአገረ ገዥ ኒኪ ሄሊን፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርነት ሹመት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ትናንት አፅድቋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ካቀረቡት የዕጩ ባለሥልጣናት ዝርዝር በምክር ቤቱ ይሁንታ ሲሰጣቸው ኒኪ ሄሊ ገና አራተኛ መሆናቸው ነው።

ሪፖብሊካኖች የሹመቱን ማፅደቅ ሂደት በማጓተትና ሀገሪቱን በማክሰር ዴሞክራቶቹን ይከስሳሉ፤ ዴሞክራቶቹ ደግሞ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ሹማምንቶችን ሥነ ምግባር ሕገ መንግሥቱ በሚያዝዘው መሠረት እያጣራን ነው ይላሉ።

ማይክል ባውማን ሴኔቱ ሥራውን እያከናወነ ካለበት ከተወካዮች ምክር ቤቱ የላከውን ዘገባ ትዝታ በላቸው ታቀርባለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሴኔቱ ከትራምፕ ዕጩዎች የአራቱን አፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00

XS
SM
MD
LG