በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ትራምፕ - ስለ ጆን ሉዊስ


በዩናይትድ ስቴትስ የጆርጂያው ተወካይ ጆን ሉዊስ
በዩናይትድ ስቴትስ የጆርጂያው ተወካይ ጆን ሉዊስ

በዩናይትድ ስቴትስ የጆርጂያው ተወካይ ጆን ሉዊስ ከነገ በስቲያ ዓርብ በሚካሄደው የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ላይ እንደማይገኙ ያላቸውን ዕቅድ ተከትሎ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሲቪል መብቶች ታጋዩ ላይ የትችት ናዳ አውርደዋል።

ኮንግሬስ ማን ሉዊስ “ወሬ ብቻ እንጂ እርምጃ መውሰድ ወይም ውጤት ማስመዝገብ አይሆንላቸውም” ሲሉም ትራምፕ ተችተዋል።

እንደራሴ ጆን ሉዊስ “ወንጀል የበዛበትንና እየተፈረካከሰ ያለውን ወረዳቸውን ማስተካከል ሲገባቸው ስለ ምርጫው ውጤት በሀሰት ምሬት ያሰማሉ” በማለትም ወርፈዋቸዋል።

ውዝግቡ ከተፈጠረ ወዲህ በተመራጩ ፕሬዚዳንት የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ላይ እንደማይገኙ የሚገልፅ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከ50 በላይ ደርሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዶናልድ ትራምፕ - ስለ ጆን ሉዊስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00

XS
SM
MD
LG