በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ብዙ ቅርንጫፎች ያሉትና ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ ዳቦ በማምረትና በመሸጥ ንግድ ላይ የቆየው “ሸዋ የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ” በዳቦ ላይ እጥፍ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል።
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች የተለያዩ ከተሞች ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂ ኃይሎች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።
የመከላከያ ሰራዊቱ ግጭቱ ወደተቀሰቀሰባቸው የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንና ወደ በሰሜን ሸዋ ዞኖች ከገባ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተኩስ መቆሙን የመከላከያ ሚኒስቴር ም/ኢታማዦር ሹም ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ኒፕሲ ሃስል ወይም ኤርሚያስ አስገዶም፣ ከሙዚቃ ሞያው በላይ በጎ ተግባሩ በሕይወታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እንዳሳደረባቸው ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተዘጋጀው የሻማ ማብራት ሥነ - ሥርዓት ላይ የታደሙ ወጣቶች ይናገራሉ
ኒፕሲ ሃስል ወይም ኤርሚያስ አስገዶም፣ ከሙዚቃ ሞያው በላይ በጎ ተግባሩ በሕይወታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እንዳሳደረባቸው ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተዘጋጀው የሻማ ማብራት ሥነ - ሥርዓት ላይ የታደሙ ወጣቶች ይናገራሉ። ባለፈው ሳምንት እሁድ ሎስ-አንጀለስ ውስጥ በስድስት ጥይት የተገደለው ኤርትራ - አሜሪካዊው የሙዚቃ ሰው ኒፕሲ ሃስል ፣በወጣትነቱ ያከናወነው በጎ ተግባር በሚሊዮን ወጣቶች ልብ ውስጥ የብርሃን አሻራ መተውን በመግለፅ እማኝነታቸው ሰጥተውለታል። (ካሜራ አቢሰን)
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሐመድን ስለ መገናኛ ብዙሃን ሚናና፤ የሚመራው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ(ኦ.ኤም.ኤን) ስለሚያከናውነው ሥራ ጠይቀነዋል።
“ይህንን ዓለም እንኑርበት አንኑርበት ዋስትና የለንም። ስለዚህ ዛሬ ያለችንን ቀን ተሳስበንና ተፋቅረን እንድንኖር እግዚያብሔር ትልቅ መልዕክት ያለው ይመስለኛል” ይህንን ያሉት በአይሮፕላን አደጋው ሕይወቱን ያጣው የ27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው እናት ወ/ሮ ሚልካ ይማም ናቸው።
በኬንያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሲያቀርቡ በእጃቸው ስለያዟት “ጭራ” ጉዳይ ተጨዋውተዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ፤ “የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ለአባቴ የሰጧቸው ጭራ እስከመጨረሻ የሕይወት ፍፃሜያቸው ድረስ አብሯቸው ነበር” ሲሉም ነግረዋቸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ የነበረው ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ ልጃቸው ለማግባት በዝግጅት ላይ እንደነበር ገልፀዋል።
ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚገኘው ለገጣፎ አካባቢ ከአርሶ አደር ላይ መሬት ገዝተው የገነቡት ቤት “ሕገወጥ ነው” በሚል እንዲፈርስ መደረጉ “በአደባባይ የተፈፀመብን በደል ነው” ሲሉ ነዋሪዎች እየገለፁ ናቸው።
በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር በአማራና በቅማንት መካከል ትናንትና ዛሬ ተባብሷል የተባለውን ግጭት ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት መተማ መግባቱን የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ቢሮና መከላከያ አስታወቀ።
የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርና ስለ መከላከያ ዩኒፎርም ተጠይቀዋል። ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ጎንደርና ትግራይ መከላከያው የወሰደው እርምጃና ያሳየው ትዕግስት አድሎአዊ ነው ስለመባሉም ተጠይቀዋል።
-መከላከያ በበኩሉ ታጣቂዎች "መከላከያ ሰራዊት" ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብሏል
በቤንሻንጉል ጉምዝ ማኦኮሞ ወረዳ ውስጥ በአልሚዎች የእርሻ ቦታ በቀን ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደነበር የሚናገሩ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው በታጣቂዎች ጥቃት እንደረሰባቸው የተወሰኑት ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ድሬዳዋ በተጠራች ቁጥር ስለ ነዋሪዎቿ ስብጥርና ሰላም “የፍቅር ከተማ” የሚል ሃረግም እንደ ዓርማ ሁሉ አብሮ ይነሳላታል። ከጥቂት ወራት ወዲህ ግን የግጭት ሁኔታዎች ብልጭ ድርግም ሲሉ ይስተዋላል።
በድሬደዋ ከተማ ከሰባት ዓመት በፊት የተጀመረ የውኃ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ በመዘግየቱ የሚጠጣ ውኃ አገልግሎት ችግር መኖሩን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክቱ በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።
ግድያ እና መፈናቀል እንዲቆም የሚጠይቅ ሰለፍ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተደረገ። ሰልፈኞቹ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲያመጣ ጠይቀዋል።
በሶማሌ ክልል እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ሰዎች በሕግ ፊት ቀርበው ሲዳኙ ማየት ትልቁ ምኞቱ እንደሆነ አንድ ቀድሞ በእነዚህ ቦታዎች ታስሮ የነበረ ወጣት ተናገረ።
በተለያዩ ባለሞያዎች ተቃውሞ ሲቀርብበት የቆየው የአልኮል መጠጦች ገደብ አልባ ማስታወቂያና የሲጋራ አጫጫስና ማስታወቂያ አለጣጠፍ ላይ ገደብ የሚጥል ረቂቅ ዐዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ፀደቀ።
ተጨማሪ ይጫኑ