በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት መከላከያ ሰዎችን ተኩሶ መግደሉን ነዋሪዎች ገለፁ


ከማኅበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ላይ የተገኘ
ከማኅበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ላይ የተገኘ

-መከላከያ በበኩሉ ታጣቂዎች "መከላከያ ሰራዊት" ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብሏል

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት በተባለ ቀበሌ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት በተተኮሰ ጥይት 27 ሰዎች መመታታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የዓይን እማኝ መሆናቸውን የተናገሩ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለፁ። ግድያውንም በመቃወም ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የሆስፒታል ምንጮች ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ነግረውናል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው በአካባቢው በመንገድ ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያን አጅቦ በመውጣት ላይ በነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የታጠቁ ሰዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገልፀዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት መከላከያ ሰዎችን ተኩሶ መግደሉን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:03 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG