በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዳቦ ነገር!


ፎቶ ፡ ሮይተርስ
ፎቶ ፡ ሮይተርስ

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ብዙ ቅርንጫፎች ያሉትና ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ ዳቦ በማምረትና በመሸጥ ንግድ ላይ የቆየው “ሸዋ የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ” በዳቦ ላይ እጥፍ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል።

በዳቦ ዋጋ ላይ እስካሁን ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩት ከመንግሥት ጋር በነበራቸው ስምምነት የስንዴ ዋጋ እየተደጎሙ በመቆየታቸው እንደነበረ የድርጅቱ ባለቤቶች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀው ከአራት ዓመት በፊት በነበረው የዋጋ ተመን ስምምነት አሁንም ድረስ መቆየታቸው ለኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም ድርጅቱን በኪሣራ ከመዘጋት ይልቅ ከትስስር ወጥተው በራሳቸው መንገድ መቀጠል መምረጣቸውን አመልክተዋል።

“ሸዋ ዳቦ ጥሩ ምግባር ከነበራቸው የንግድ ድርጅቶች አንዱ ነበር” ያለው የንግድ ሚኒስቴር ድርጅቱ “ከትስስር ወጥቼ በነፃ ገበያ እሸጣለሁ” የማለት መብት እንዳለው ጠቅሶ “...ነገር ግን በተለይ በዚህ ወቅት በትስስር ውስጥ ሆኖ ቢሠራ መልካም ነበር” ብሏል።

“የሰዉን የዳቦ ችግር ለማቃለል ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን እንጠቀማለን” ብሏል የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

የዳቦ ነገር!
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:42 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG