በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አብራው ከምትሠራ ካፒቴን እጮኛው ጋር ሊጋቡ እቅድ ይዘው ነበር" -የአብራሪ ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ የነበረው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ የነበረው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ የነበረው ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ ልጃቸው ለማግባት በዝግጅት ላይ እንደነበር ገልፀዋል።

“እግዚያብሔር ሰጠ እግዚያብሔር ነሳ” - በሚል የፈጣሪያቸው ቃል እየተፅናኑ እንደሚገኙ የገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ከትናንት በስቲያ ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ የእርሳቸው ልጅ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ያለቁበት አደጋ በመሆኑ በቦታው ላይ በስማቸው የመታሰቢያ ሃውልት ቢቆም ምኞታቸው እንደሆነ ተናገሩ።

ምክኒያታቸው ደግሞ ከአደጋው ከፍተኛነት የተነሳ የልጃቸውን አስክሬን አግኝተው መቅበር እንደማይችሉ ስለተረዱ ቢያንስ ለመታሰቢያ እንኳን “ስሙ በቦታው ቢሰፍርልኝ” እወዳለሁ ብለዋል።

(ጽዮን ግርማ ማምሻውን ሐዘን ከተቀመጡበት አዳማ በስልክ አነጋግራቸዋለች- ቃለምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG