በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የተጋጩትም ፤የተታኮሱትም በሁለቱም በኩል ያሉ ታጣቂዎች ናቸው"- የመከላከያ ሚኒስቴር ም/ኢታማዦር ሹም ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው


የመከላከያ ሰራዊቱ ግጭቱ ወደተቀሰቀሰባቸው የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንና ወደ በሰሜን ሸዋ ዞኖች ከገባ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተኩስ መቆሙን የመከላከያ ሚኒስቴር ም/ኢታማዦር ሹም ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች የሰዎችን ነፍስ የቀጠፈ እና የንብረት ያወደመ ግጭት ተፈጥሯል፡ግጭቱን ተከትሎ በፌዴራል መንግስት ስር ያሉት የጸጥታ እና ደህንነት ሃይሎች በጊዜ ርምጃ አለመውሰዳቸው ተጠቅሶ ወቀሳ በዝቶባቸዋል፡፡
ወቀሳው ከደረሳቸው ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የመከላከያ ሚኒስትር ኋይሉን ወደ ተጠቀሱት ቦታዎች ከላከ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተኩስ መቆሙን የመከላከያ ሚኒስቴር ም/ኢታማዦር ሹም ጽ/ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
"ግጭቱ የተከሰተው በሕዝቦች መካከል አይደለም፣ የተጋጩትና የተታኮሱት በሁለቱም በኩል ያሉ ታጣቂዎች ናቸው። " ሲሉ የሚሟገቱት ሃላፊው በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG