በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰባት ዓመት ያስቆጠረው የድሬደዋ ውሃ ፕሮጀክት


በድሬደዋ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ከባንቧው ውስጥ እንዲህ ያለ ውሃ እንደሚወጣ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በድሬደዋ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ከባንቧው ውስጥ እንዲህ ያለ ውሃ እንደሚወጣ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በድሬደዋ ከተማ ከሰባት ዓመት በፊት የተጀመረ የውኃ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ በመዘግየቱ የሚጠጣ ውኃ አገልግሎት ችግር መኖሩን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክቱ በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።

ተይዞ የነበረው በጀት ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለፕሮጀክቱ ይሠራል የተባለ የኤሌክትሪክ አገልግሎትም በመዘግየቱ ለጀኔሬተር በወር በሚሊዮን የሚቀጠር ገንዘብ እየወጣ እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፕሮጀክቱ ሥራ ለሁለት ዓመታት መዘግየቱን አምኖ “ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ነው” ነው ብሏል። በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።

ከፕሮጀክቱ በጀት ላይ የ46 ሚሊዮን ብር ሥራ ለማከናወን የአገልግሎት ክፍያ የተፈፀመለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድሬዳዋ ዲስትሪክት በበኩሉ “በተያዘው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እየሠራሁ ነው፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ አጠናቅቃለሁ” ብሏል። (ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ሰባት ዓመት ያስቆጠረው የድሬደዋ ውሃ ፕሮጀክት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG