በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ምርጫ ቦርድ 'ምርጫ' የማራዘም ሥልጣን የለውም" - ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ


የምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ
የምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ

በመጭው ዓመት ሊደረግ የታቀደውን ጠቅላላ ምርጫ ጊዜ ፤ መራዘምም ሆነ አለመራዘም በተመለከተ ለማንም መግለጫ ሰጥቶ እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

"ቦርዱ ሰላም ሳይኖር ምርጫ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው” አለ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨውም “የሃሰት ወሬ ነው” ብሏል። ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲካሄድ ለማድረግ ዝግጅቱን እያፋጠነ እንደሚገኝ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

“ምርጫውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማከናወን የማያስችል ሁኔታ ቢፈጠር እንኳን ተጠሪ ለሆንለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እናሳውቃለን እንጂ በራሳችን ምርጫ የማራዘምም ሆነ የመሠረዝ ሥልጣን የለንም” ሲሉ የምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ “ምርጫ ቦርድ ምርጫውን አራዘመ” በሚል በማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ ዛሬ የተሠራጨውን ዘገባ መሠረት አድርጋ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

"ምርጫ ቦርድ 'ምርጫ' የማራዘም ሥልጣን የለውም" - ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:21 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG