የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ፣ ከሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፦
አዲስ አበባና የዩናይትድ ስቴትሷ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ የእህትማማች ከተሞች ስምምነታቸውን አደሱ።
ሰሞኑን በኦሮምያ፣ በድሬዳዋና በሀረሪ ክልሎች በደረሱ ጥቃቶች 86 ሰዎች መገደላቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትናንት ባሰሙት ንግግር አስታውቀዋል።
ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ አልሲሲ በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ያደረጉት ውይይት መግባባት የተሞላበት አንደነበር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ አስታወቁ፡፡
በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር እንደሚናጋገሩ የገለፁት የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኅዳሴውን ግድብ ግንባታ የሚያቆም ምንም ኃይል የለም ብለዋል፡፡
"የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ያሸነፉት የኖቤል ሽልማት አፍሪካውያን ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ነው" ሲሉ ሙሳፋኪ ማሃማት ተናገሩ።
የአማራ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ምክር ቤት ሰሞኑን ይፋ ያደረጋቸው ክልከላዎችና ውሳኔዎች መነሻ በአንዳንድ አካባቢዎች የቀጠለው የፀጥታ ችግር መሆኑን አንድ ከፍተኛ የክልሉ ባለሥልጣና ተናግረዋል፡፡
"በህወሓት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣለት ሳይሆን ከመጣበት፣ ህዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው" ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል። “ለዚህም ምክንያቱ መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅም መኖሩና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ያሸነፉት የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተበረከተ የአደራ ሽልማት ነው ሲል ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ታላቁ ቤተመንግሥት የተገነባው አንድነት ፓርክ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ከጥቂት ቀናት በኋላም ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የፅህፈት ቤታቸውን ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጡ።
በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ዘግበናል፡፡
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡ ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገርም ትክክል አይደለም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡ የተወሰ ጊዜም እንደሚወስድ ይታወቅ እንደነበርም አብራርተዋል፡
ከከፋ ህዝብ የምንማረው ብዙ ነገር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አካባቢውን መጠበቁን እና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ማኖሩን አድንቀዋል፡፡
“ኢትዮጵያን የማሳነስ ልምምድ ለልጆቻችን አናወርስም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደዚሁም የተለያዩ ሃይማኖቶች አገር መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው ሁሉም ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቅ ሃገር ለመገንባት እንደሚሠራም አብራርተዋል።
ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሁለት የረድዔት ሠራተኞች የተገደሉበትን ከአንድ ሣምንት በፊት የተፈፀመውን ጥቃት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አውግዟል።
የተሻለ እንጂ የከፋ ዘማን ተመልሶ እንዳይመጣ እውነተኛ ሽግግር ለልጆቻችን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ዜጎቿ የሚፈልጓትን ሀገር ለመገንባት ቁልፉ ያለው እየተወሰዱ ባሉ የማሻሽያ ዕርምጃዎች ላይ መሆኑን ከመቼውም ጊዜ በላይ አምናለሁ ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር አስታወቁ፡፡
ሁሉም የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት በጋምቤላ ክልል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለጊዜው ማቋረጣቸውን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ አስታወቁ፡፡
ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰሞኑን በተከሰተው መጤ-ጠል ጥቃት ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተናገሩ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት እየተፈፀሙ ያሉ ሁከቶችን በብርቱ ቃላት አውግዞ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ተጨማሪ ይጫኑ