ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮሪያ ጃፓንና እሥራኤል ያደረጉት ጉብኝት ለ2012 የተያዘውን ሦስት ሚሊዮን የሥራ ዕድል የመፍጠር ዕቅድ የሚያግዝ መሆኑን ቃል አቀባያቸው እስታወቁ።
"ህወሃትን የመሳሰሉ ፓርቲዎች ዳግም ወደ ሥልጣን ለመመለስ እንደ ኦነግ ካሉ ድርጅቶች ጋር አዲስ የፖለቲካ ግንባር እየፈጠሩና መሰል ድርጅቶችን እያሰባሰቡ ነው" ሲሉ የኢዴፓ ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የፓርቲው የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ተናግረዋል።
ቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ለሚያስችል ጊዜ መራዘም እንዳለበት በአቶ አዳነ ታፈሰ የሚመራው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ አሳሰበ።
“እኛ የሠራነውና የመጣው ውጤት የተራራቀ ነው” ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ዛሬም የቅሬታ ቅጽ ሲሞሉ ውለዋል። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ትምሕርት ቤቶች በፈተና ሂደቱ ላይ የነበረው ችግር ሳይስተካከል ውጤቱ ይፋ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።
የፊታችን 2012 ዓ.ም መገባደጃ ላይ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ በሕገመንግሥቱ በተቀረፀው ማዕቀፍና ጊዜ እንዲካሄድ የገዥው ኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቋም መያዙ ተገልጿል።
በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ሀገር ቤት ካሉ በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር የተባበሩበት የሴት ተማሪዎች የኮምፒውተር ኮዲንግ ወይንም ቅመራ ሥልጠና ተጠናቋል፡፡
ሃዲያ ዞን በደቡብ ክልል ችግር ከተፈጠረባቸው አካባቢዎች ጋር ተዳምሮ መጠቀሱና አስተዳዳሪውም መታገዳቸው ተጨባጩን ሁኔታ ያላገናዘበ እርምጃ ነው ሲሉ የዞኑ የሃገር ሽማግሌዎች ቅሬታ አሰምተዋል።
ሰኔ 15 ቀን በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙት ግድያዎች ግንኙነት እንዳላቸው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡
ለውጡን የሚመራው ስብስብ በሰብዓዊ መብት ላይ ያልው አቋም አልተቀየረም ሲሉ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ገዥ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ዴኢህዴን/ ጉባዔውን ዛሬ አጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብረዋል።
አሁን ያለው ህገ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም ሲሉ አንድ የቀድሞ የተቃዋሚ መሪና የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡ ህገ መንግሥቱ ለፌዴራሊዝም ሳይሆን ለኮንፌዴሬሽን ወይም ለመነጣጠል የሚሆን ነው ሲሉ ነው የተቃዋሚው መሪው አቶ ልደቱ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት፡፡
የደቡብ ክልሉን ቀጣይ አከላለልና ዕጣ ፈንታ በተመለከተ የተለያዩ አማራጮች የቀረበበት ጥናት ውጤት ዛሬ በምሁራን ውይይት ተደርጎበታል።
በደቡብ ክልል ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተሻለው አማራጭ አሁን ባለው አንድነት መቀጠል መሆኑን ለአለፉት ሰባት ወራት ጥናት ያካሄደው ገለልተኛ ቡድን አጥኝ አስታወቀ።
ሱዳንን እየመሩ ያሉት የጦር አዛዦችና ተቃዋሚዎቹ፣ ዛሬ የሰላም ሥምምነት ተፈራረመዋል፡፡
“ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻና ብጥብጥ ከሚቀሰቅሱ የዳያስፖራ አባላት የተወሰኑት ዩናየትድ ስቴትስ የሚገኙ ናቸው” ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ አምባሳደር ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትናንትና ማብራሪያ ዋንኛ ነጥብ መንግሥታቸው ህጋዊ ባልሆነ አካሄዶች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር መጠቆማቸው ነው ይላሉ አንድ አንጋፋ የተቃዋሚ መሪ፡፡
“ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ የሚቸግርበት ጊዜ እንዳይመጣ ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሰሞኑ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ዛሬ ለፓርለማው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አሳሰቡ።
ሰሞኑን በጠባቂያቸው የተገደሉት የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ጡረተኛው ጄነራል ገዛዒ አበራ አስከሬን ዛሬ በሚሊኒዬም አዳራሽ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
በአማራ ክልል አመራር አባላትና በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ላይ የተፈፀመው ግድያ “ተገለገሏት ኢትዮጵያና በተቋማቱ ላይ እንደተፈፀመ የሚቆጠር ነው” ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ