ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።
ዛሬ በመላው ዓለም ለመፀነስ ከሚችሉ ሴቶች መካከል 800 ሚሊዮን የሚሆኑት ላልታሰበበት እርግዝና እንደሚጋለጡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
“የጡት ካንሰር በወቅቱ ተመርምረው ከተደረሰበት ህይወትን ማትረፍ እንደሚቻል እኔ ምስክር ነኝ፥ እህቶቼ ችላ አትበሉ።” ወይዘሮ ምስራቅ ገሠሠ
በቂ የትምህርት ዕድል የማያገኙ ሴት ልጆች የሚጋለጡበትን የሥቃይ ህይወት ትኩረት የሚስብ አዲስ ሪፖርት በተባበሩት መንግሥታት ድርጁቱ ዓለም አቀፍ የሴት ልጆች ቀን ወጥቷል።
በኢትዮጵያ የእሥልምና አማኒያን ማህበረሰብ ውስጥ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች “የሃገሪቱ መንግሥት በእስልምና ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ ነው” ባሉት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ሠልፎችን እያደራጁ ነው።
በቀድሞው መሪ የአርባ ዓመታት አምባገንን አገዛዝ ላይ ዓመፅ ከተቀሰቀሰ ከሰባት ወራት በኋላ ዛሬ ሐሙስ የሽግግሩ መንግሥት ወታደሮች ጋዳፊን የገደሏቸው በትውልድ ከተማቸው በሲርቴ ላይ ባካሄዱት የመጨረሻ ጥቃት ነው።
ከዓለም እጅግ ተፈላጊው አሸባሪ ኦሳማ ቢን ላድን ተገድሏል። የሃምሳ አራት ዓመቱ ሽብርተኛ መሪ ትናንት ዕሁድ ፓኪስታን ግዛት ውስጥ በሚገኝ ግቢ በዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች መገደሉን ይፋ ያደረጉት ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ናቸው።
በዩናይትድ ስቴትስ የህግ ትምህርት በመከታተል ላይ ያሉ ሁለት ኢትዮጲያውያት በአፍሪካ ሴቶች ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ጥናታዊ ገለጻ አደረጉ።
"ዕምቢ ለነፃነቴ" ብሎ የግብፅ ወጣት ሰንጎ የያዛቸው ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል።
በዓለም ዙሪያ ከሃምሣ በሚበልጡ ሀገሮች ከሃያ ሰባት ሚሊዮን በላይ በጦርነቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች አሉ። ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ግማሹ ማለትም አስራ ሦስት ሚሊዮኑ ህፃናት ናቸው።
በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ይዞታ ምን ይመስላል? በፀሐይ ኃይል በሚሠሩት መጠቀምስ ተለምዷል? -- ውይይት ከሶላር በረከት መሥራች ጋር፡፡
ለተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች በጠቅላላ ፥ ከመወሰኛው ደግሞ ለአንድ ሦስተኛው፣ እንዲሁም ብዙ ትኩረት ለሣቡ የአገረ ገዥዎችም ምርጫዎች ህዝቡ ድምፁን ይሰጣል።