በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምርጫ እንጂ በነሲብ አይሁን፡-


ዛሬ በመላው ዓለም ለመፀነስ ከሚችሉ ሴቶች መካከል 800 ሚሊዮን የሚሆኑት ላልታሰበበት እርግዝና እንደሚጋለጡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።


ከነዚህ መካከል ግማሽ የሚሆኑት ፅንሣቸውን ለማቋረጥ እንደሚዳረጉ የመንግሥታቱ ድርጅት የሥነ-ህዝብ ቢሮ UNFPA ባወጣው የዓለም የህዝብ ሁኔታ ግምገማ ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ይፋ ያደረገው በአፍሪካ አሕጉር ላይ ያተኮረው ሪፖርት ያነጣጠረው በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ነው፡፡
የዓመታዊ ሪፖርቱ ርዕስ በእንግሊኛ “By Choice, Not By Chance: Family Planning, Human Rights and Development” ይላል፡፡ በአማርኛ “በምርጫ እንጂ በነሲብ አይሁን፡- የቤተሰብ ምጣኔ፣ ሰብዓዊ መብቶችና ልማት” የሚል ይሆናል፡፡

ሪፖርቱ በዚህ ረገድ አፍሪካ ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች እና በአጭር ጊዜም ያስመዘገበችው ስኬት ሊያመለክት ሞክሯል፡፡

ተግዳሮቶች ብሎ ከደረደራቸው መካከል በዓለም ከእርግዝና ጋር ተያይዞ ከሚደርሰው የሞት አደጋ ሃምሣ አምስት ከመቶ የሚሆነው በአፍሪካ አሕጉር የሚደርስ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ቢዳረስ ሀገሮቹ ለእናቶች እና ለህፃናት ጤና ጥበቃ ወጪአቸውን በዓመት በአሥራ አንድ ቢሊዮን ዶላር ይቀንሳል ሲል ይኸው ሪፖርት አስታውቋል።

UNFPA በዘንድሮ የዓለም የሥነ ህዝብ ይዞታ ሪፖርቱ የቤተሰብ ምጣኔ ግዙፍ የሆነ የምጣኔ ሃብት ጠቀሜታ እንዳለውም አስገንዝቧል።

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ የአዲስ አበባ ዘገባ እና ቆንጂት ታየ ካዘጋጀችው ሪፖርት ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG