በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥቅምት አንድ ዓለም አቀፍ የሴት ልጆች ቀን ነው


በቂ የትምህርት ዕድል የማያገኙ ሴት ልጆች የሚጋለጡበትን የሥቃይ ህይወት ትኩረት የሚስብ አዲስ ሪፖርት በተባበሩት መንግሥታት ድርጁቱ ዓለም አቀፍ የሴት ልጆች ቀን ወጥቷል።


please wait

No media source currently available

0:00 0:09:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

INTERNATIONAL DAY OF THE CHILD GIRL.

ፕላን ኢንተርናሽናል የተባለው የህፃናት ደህንነት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ባለም ዙሪያ ዕድሜቸው ከአሥራ አንድ እስከ አሥራ አምስት የሆኑ ሰላሣ ዘጠኝ ሚሊዮን ሴት ልጆች ትምህርት ቤት የመግባት ዕድል ያላገኙ መሆናቸውን ያመለክታል። ችግሩ በአፍሪካ የበረታ መሆኑንም ያሠምርበታል።
የዛሬውን ዓለም አቀፍ የሴት ልጆች ቀን ምክንያት በማድረግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የትምህርት ዕድል ውሱን ሲሆንባችው ሴቶች ህይወታቸውን ሙሉ ጉዳት ላይ ለሚጥሏቸው ችግሮች እንደሚጋለጡ አበክረው አስገንዝበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ዕለቱን አስደግፎ ባወጣው ሪፖርት የሴት ልጅን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች የሚገፍ ለሁለንተናዊ ሥቃይ የሚዳርግ የመብት ጥሰት ነው ሲል ኮንኖታል።
በኢትዮጵያ ያለዕድሜ መዳርን ለማስቀረት መጠነ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እና ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀረፈ ቢሆንም አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚካሄድ በመሆኑ ብርቱ ሥራ እንደሚጠይቅ ይታወቃል።
በኢትዮጵያ የአክሽን ኤድ የሴቶች ልማት መርሃግብር አስተባባሪ ወይዘሪት ቤቴል ተረፈ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ያለውን ያለዕድሜ መዳር ችግር አድማስ የማስወገድ ጥረቱን እና ወደፊት የሚጠበቀውን ሥራ ያብራራችበትን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
XS
SM
MD
LG