በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ኤምባሲ የዳይቨርሲቲ ቪዛ አመልካቾች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ


አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የብዙኃንን ትኩረት ከሚስበው የአሜሪካ የቪዛ ሎተሪ ወይም የዳይቨርሲቲ ቪዛ መርኃ ግብር ጋር በተያያዘ ወቅት በርካታ የማታለያ የኢ ሜይል መልዕክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እየተዘዋወሩ በመሆኑ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (ዲቪ) አመልካቾች በእነዚህ የማታለያ የኢ ሜይል መልዕክቶች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ፡፡

የኤምባሲው የየኮንሱላር ቢሮ ድሬክተር አቢጌል ረፕ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ኤምባሲው ለአመልካቾች ከአሁን ቀደምም ሎተሪውን አግኝታችኋል ብሎ በኤሌክትሮኒክ ሜይል አብስሮ እንደማያውቅ አስታውሰው አሁንም በዲቪ 2012 በኢሜልም ሆነ በደብዳቤ እንደማያስታውቅ አሳስበዋል።

የአሜሪካ ኤምባሲም ሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢንተርኔት፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላለፍያ (ሐዋላ) ወይም በኢ ሜይል ምንም ዓይነት ክፍያ እንዲከፍሉ በፍፁም እንደማይጠይቅና ከዲቪ መርኃ ግብር ጋር በተያያዘ ክፍያ ይፈጽሙ ዘንድ የሚጠይቅ ማንኛውም የኢ ሜይል መልክዕክት ለማጭበርበር የታለመ መሆኑን አጥብቀው አስገንዝበዋል።

የአሜሪካ ኤምባሲዋ ባለስልጣን ለአሜሪካ እና ህዝቡዋ ፕሮግራም የሰጡትን ሰፋ ያለ ማብራሪያና ማሳሰቢያ ያድምጡ

XS
SM
MD
LG