በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ሴቶች ሰብዓዊ መብቶች


በዩናይትድ ስቴትስ የህግ ትምህርት በመከታተል ላይ ያሉ ሁለት ኢትዮጲያውያት በአፍሪካ ሴቶች ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ጥናታዊ ገለጻ አደረጉ።

የሴቶች ሰብዓዊ መብት በአፍሪካ በሚል ርዕስ በቅርቡ በዚህ በዋሽንግተን በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ውስጥ አንድ ገለጻ ተደርጎ ነበር ። ገለጻውን ያስተባበሩት በዋሽንግተን የGEORGETOWN ዩኒቨርስቲ የህግ ማዕከል የሚያካሂደው በእንግሊዝኛ አህጽሮት መጠሪያው LAWA LEADERSHIP AND ADVOCACY FOR WOMEN OF AFRICA የተባለው መርሃ ግብር ነው ።

ገለጻውን ካደረጉት መካከል ሁለቱ ኢትዮጲያውያት ወጣት በዩኒቨርስቲው በነጻ ትምህርት ዕድል አግኝተው ከፍተኛ የህግ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ወጣቶች ነበሩ።

አንዲቱ ወይዘሪት ማክዳ ተሰማ በሴቶች ልጆች ግርዛት ወይዘሪት ሰላማዊት ተስፋዬ ደግሞ ወደአረብ ሀገሮች በቤት ሰራተኝነት የሚሄዱ ኢትዮጲያውያት ችግሮች በተመለከተ ባካሄዱዋቸው ጥናቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

ዝርዝሩን ያድምጡ

XS
SM
MD
LG