በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤትና የአገረ ገዢዎች ምርጫ ነገ ማክሰኞ ይካሄዳል።


ለተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች በጠቅላላ ፥ ከመወሰኛው ደግሞ ለአንድ ሦስተኛው፣ እንዲሁም ብዙ ትኩረት ለሣቡ የአገረ ገዥዎችም ምርጫዎች ህዝቡ ድምፁን ይሰጣል።

ዲሞክራቶች በሁለት ሺህ ስድስት ሁለቱንም ምክር ቤቶች በሁለት ሺህ ስምንት ደግሞ ዋይት ሐውስን እንደተቆጣጠሩ ሲታወቅ በዚያ መልክ የመቀጠሉ ነገር ግን አጠራጥሯል፡፡

በዚህ ድባብ መሃል ደግሞ ቅዳሜ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ታዋቂ የፖለቲካ ኮሜዲያኖች የጠሩት "RESTORE SANITY" (“ኧረ ልቦና ይስጠን” ብለን በግርድፉ ብንተረጉመው)፥ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ ስብሰባው በተወጠረው የወቅቱ የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተንገፈገፉ በርካታዎችን የሳበ ነበር።

"በህዝቡ ዘንድ የተነዛው ፍርሃት አግባብነት የለውም፤ ዘና እንበል" የሚል አጠቃላይ መንፈስ የያዘ ነበር። ያዘጋጁት "ዘ ዴይሊ ሾው" የተባለ ሽሙጥ አዘል ዜና አቅራቢው ጆን ስቲዋርትና መሰል ፕሮግራም ያለው የኮልበርት ሪፖርቱ ስቲቭን ኮልበርት ናቸው። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG