በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፃዊያን አብዮትና አንድምታው


"ዕምቢ ለነፃነቴ" ብሎ የግብፅ ወጣት ሰንጎ የያዛቸው ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል።

ለአስራ ስምንት ቀናት ከካይሮ እስከ አሌክሳንድሪያና በመላው ግብጽ የተቀጣጠለው ፀረ-መንግሥት ዓመፅ ዓርብ ዕለት ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ስልጣናቸውን ለሀገሪቱ ጦር ሠራዊት እንዲያስረክቡ አስገድዷቸዋል።

በሰሜን አፍሪካዊቱ ሀገር በወጣቶች አንቀሳቃሽነት የተጀመረው ህዝባዊ አመፅ ለሰላሣ ዓመት የገዛውን የፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክን አስተዳደር ነው ከስልጣን ያስወገደው። ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣን ያወረደው ይህ ህዝባዊ አመፅ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት ስቦ ሰንብቷል።

የኢትዮጵያ ወጣት፥ ባጠቃላይም ወደሰባ ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝበት ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኘው የአፍሪካ ክፍል በሕዝባዊ ንቅናቄና ንቃት ዙሪያ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከግብፅና ከቱኒዚያ የወጣቶች እንቅስቃሴስ ምን ይማራል?

መስታወት እነዚህን ነጥቦች ይዞ ለውይይት የጋበዛቸው ሁለት ወጣቶች፥ ጃዋር ሲራጅ፥ የስታንፈርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅና የፖለቲካ ተንታኝ፥ ካሣሁን አዲስ ደግሞ ቀድሞ በአዲስ አበባ የዋሽንግተን ፖስት የመስክ ዘጋቢ የነበረ፤ በደረሰበት ጫና አገር ለቆ የወጣ ወጣት ነው።

ለዝርዝሩ ውይይቱን ያዳምጡ ።

XS
SM
MD
LG