ወይዘሮ አበበች ጎበና ፥ የክብር ዶክተር አበበች ጎበና የኢትዮጵያ ማዘር ቴሬዛ ፥ ወዘተ በሚሉ መጠሪያዎች ይታወቃሉ . በእንግሊዝኛ አህጽሮቱ ሲድ ተብሎ የሚታወቀው መሠረቱን እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገ የኢትዮጲያውያን የሽልማት ድርጅት ማህበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጲያ ዘንድሮ ካከበራቸውና ከሸለማቸው ለማህበረሰባቸው ታላላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጲውያን መካከል አንዱዋ ነበሩ ።
በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ በኢትዮጲያ በደረሰው ድርቅና ረሃብ ወቅት ወደግሸን በሄዱበት ጉዞአቸው በረሃቡ ህይወቱዋ ያለፈ እናቱዋን ጡት ስትጠባ ያገኙዋትን ህጻን አንስተው ወደቤታቸው ይዘው ከሄዱ ወዲህ ህይወታቸውን ወላጅ ለሌላቸው ህጻናት ባጠቃላይ ለችግረኞች የሰጡ የሺዎች እናት ናቸው።
ለወይዘሮ አበበች ጎበና ከሲዱ ሽልማት ስነ ስርዓት በኋላ በተደረገላቸው ተከትሎ ቨርጂኒያ በሚገኘው መዓዛ ምግብ ቤት በተደረገላቸው የአክብሮት መግለጫና ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ አግኝተናቸዋል
የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ያድምጡ