በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለተፈናቃይ ሕፃናት እንክብካቤ መመሪያ እያዘጋጀ ነው


Displaced children in Sudan
Displaced children in Sudan

በዓለም ዙሪያ ከሃምሣ በሚበልጡ ሀገሮች ከሃያ ሰባት ሚሊዮን በላይ በጦርነቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች አሉ። ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ግማሹ ማለትም አስራ ሦስት ሚሊዮኑ ህፃናት ናቸው።

ታዲያ አገሮችና የሰብዓዊ አገልግሎቶች ድርጅቶች እነዚህ ተፈናቃዮች ላሉባቸው ልዩ ችግሮች ለመድረስ የሚጠቀሙበት መመሪያየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እያዘጋጀ ነው።

ራዲካ ኩማራስዋሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጦርነቶች ውስጥ የተጠመዱ ልጆች ጉዳይ የዋና ፀሐፊው ልዩ ተጠሪ ናቸው። "በዓለም ዙሪያ - ይላሉ ኩማራስዋሪ - እነዚህ ልጆች ትኩረት ካላገኙት መካከል የሚገኙና ለአደጋ የተጋለጡ ህፃናት ናቸው። መንግሥታት እነዚህን ልጆች ለመታደግ በርታ ብለው መሥራት አለባቸው ሲሉም ያሳስባሉ።

"ባሁኑ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው ነገር ግጭት ሲፈጠር ወይም አደጋ ሲደርስ መንግሥታት ኃላፊነቱን ከራሣቸው ላይ በማውረድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንድ መላ ሊፈጥርለት ይችላል ብለው ይተዉታል። ይህ መሆን የሌለበት ነገር ነው። በቀዳሚነት ኃላፊነቱ የዚያው ሃገር መንግሥት ነው ። የሉዓላዊነት ትርጉሙም የገዛ ሲቪል ህዝቡን፣ ዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ነው። ሃገሮቹ የበለጠ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው ልናሳውቃቸው እፈልጋለን። እኛ እኮ አጋዥ እንጂ ዋናና ብቸኛ ተዋናዮች መሆን አንችልም።" ብለዋል ልዩ ተጠሪዋ፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት እያዘጋጀ ያለው መሠረታዊ መመሪያ ነው። ተፈናቃዮቹ እንደሌሎቹ ተፈናቃይ እንዳልሆኑት ልጆች ሁሉ ዕኩል መብትና ነፃነት ሊኖራቸውና ለነሱ የሚበጀውን ማድረግ የቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ሚስ ኩማራስዋሪ ያሣስባሉ። የተሻለ የኑሮ ሁኔታ፣ የደህንነታቸው መጠበቅ፥ ከወሲባዊ ጥቃት፥ በህገወጥ መንገድ ከአገር ወደአገር ከሚያጓጉዙና በግዴታ ወሲብ ንግድ ውስጥ ከሚያሠማሯቸው ኃይሎች ሁሉ መጠበቅ አለባቸው ።

መንግሥታት ተፈናቃይ ቤተሰቦች ሳይነጣጠሉ አብረው የሚኖሩበትን፥ ልጆች ትምህርት መቀጠላቸውን አስፈላጊ ሲሆንም ሥነ-ልቡናዊ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሚጠበቅባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስገነዝባል።

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG