በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሥልምና ጉዳዮች በኢትዮጵያ ዛሬ


በኢትዮጵያ የእሥልምና አማኒያን ማህበረሰብ ውስጥ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች “የሃገሪቱ መንግሥት በእስልምና ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ ነው” ባሉት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ሠልፎችን እያደራጁ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት “የአክራሪ እሥልምና መነሣሣት” አድርጎ የሚመለከተውን ለመቅጨት እየሞከረ ባለበት በዚህ ወቅት ውጥረቱ እየተጋጋለ መምጣቱ ይሰማል፡፡

ለዓርብ ሶላት ወደአወሊያ መስጊድ የሚገቡ ምዕመናን ዋናው በር ላይ በተለጠፈው መግለጫ ዙሪያ ሰብሰብ ብለው ቆመዋል፡፡ “ባለፈው በጓሮ በር ገብተዋል፤ አሁን ደግሞ ያ እንዳይደገም ጠንቀቅ ብለን እንጠብቅ” ይላል የመግለጫው ርዕስ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ “የእሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱን መንግሥት ድምፁን አጥፍቶ በቁጥጥሩ ሥር አዋለው” በማለት የሚቃወመው የአወሊያ መስጊድ ኮሚቴ ፊርማውን አኑሮበታል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ አባላት ምርጫ በየቀበሌው ይካሄድ የሚለውን ሃሣብ ኮሚቴው አይቀበልም፡፡ መካሄድ ያለበት በከተማው ውስጥ በሚገኙት መስጊዶች ውስጥ ነው ሲልም እየጠየቀ ነው፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG