በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓኪስታን ቢን ላድንን በማደኑ አግዛለች ሲሉ ዛርዳሪ ተናገሩ።


የፓኪስታን ፕሬዚደንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢን ላድን የተገደለበት ርምጃ ከሀገራቸው ጋር በጋራ የተካሄደ እንዳልነበረ አስታወቁ፥ ይሁን እንጂ ለዚህ የሰለጠነው ዓለም ጠንቅ መወገድ ያበቃው ከዩናይትድ ጋር ለአስር ዓመታት ያደረግነው ትብብር ነው ብለዋል።

ዘ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ በወጣው አስተያየታቸው የፓኪስታኑ ፕሬዚደንት ዛርዳሪ ፓኪስታን “ሽብርተኞችን በርትታ አላሳደደችም” ተብሎ ለቀረበው ትችት በሰጡት ምላሽ ሲሰጡ የኛን ያህል የአሸባሪዎች ሰለባ የሆነ አይኖርም ብለዋል።

ፓኪስታን አሉ ፕሬዚደንት ዛርዳሪ ፓኪሳታን የዩናይትድ ስቴትስ ባለልጣናት ኦሳማ ቢን ላድን ወዳለበት መራን ያሉትን የአልቃይዳ ተላላኪ ማንነት በመጠቆም ማገዝዋ ራሱ ርካታ ይሰጣታል።

የቀድሞ የፓኪስታንን ፕሬዚደንት ፐርቬዝ ሙሻረፍ በበኩላቸው ቢን ላድንን ለመከታተል የተሰራው ስራ ሳይሰምር የመቆየቱ ተጠያቂነት ዩናይትድ ስቴትስም ላይ ያርፋል ብለዋል። ከፓኪስታን ጋር ሙሉ በሙሉ በትብብር ሲሰራ የነበረው የሲ አይ ኤም ጥፋት ነው ብለዋል። ነገር ግን የፓኪስታን ጦር ሰራዊትና ደህንነት ክፍል ኦሳማ እዚያ ቦታ እንዳለ ያውቁ ነበር የሚል ሰው ካለ ይሄ ስህተት ነው ሲሉም ያስረዳሉ የቀድሞው ፕሬዚደንት።

የዓለም ቀንደኛ ተፈላጊውን አሸባሪ የዩናይትድ ስቴትስ አግኝታ በገደለችበት በፓኪስታን ዜናው ብዙዎች ነዋሪዎችን አስደንግጧል። በጣም ሰላማዊ አካባቢ ነበር አሁን ግን የአልቃይዳ በቀል ሳይመጣብን አይቀርም አሉ አንዲት ነዋሪ።

ዩናይትድ ስቴትስ ርምጃውን ፖኪስታን ውስጥ መውሰዷ ያስቆጣቸው አንዳንዶች አሉ፥ ሌሎች ደግሞ ቢን ላድን ፖኪስታን ውስጥ ለዚያውም የሀገሪቱ ምርጥ የወታደራዊ አካዳሚ ባለበት ከተማ መገኘቱ በዓለም ዓይን ሀገራችንን አሸባሪዎችን ሆን ብላ ትደብቃለች የሚል ውንጀላ ያመጣባታል ብለው የሰጉም አሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ

XS
SM
MD
LG