በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂላሪ ክሊንተን የዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው እጩ ሆነው ተመረጡ


ሂላሪ ክሊንተን በፊላደልፍያ ዴሞክራቲክ ጉባዔ
ሂላሪ ክሊንተን በፊላደልፍያ ዴሞክራቲክ ጉባዔ

ሂላሪ ክሊንተን የዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው እጩ ሆነው ተመረጡ። በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የአንድ አብይ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ በመሆንም ታሪክ ሠሩ።

ተፎካካሪያቸውን የሪፖብሊካኑን እጩ ዶናልድ ትራምፕን አስመልክቶም በንግግራቸው ጠበቅ አድርገው ባቀረቡት ነቀፌታ “ፍርሃትን በማንገስ “አሜሪካን ዳግም ታላቅ አገር እናድርግ” የሚለውን የተቀናቃኛቸውን የምርጫ ዘመቻ ንግግር ክፉኛ ነቅፈዋል።

የ42ተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ቢል ጀፈርሰን ክሊንተን ባለቤት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት እና የቀድሞዋ ሰናተር የ68 ዓመቷ ሂላሪ ክሊንተን እጩነታቸውን በተቀበሉበት ወቅት ባሰሙት በትላንቱ ምሽት ንግግራቸው አሜሪካዊያን በአንድነት ለለወጥ እንነሳ ሲሉ የተለያዩ የፖሊሲዎቻቸውን እቅዶችን አስተዋውቀዋል።

የሬፖብሊካን ፓርቲ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በሬፖብሊካኑ ጉባዔ “የአሜሪካን ችግር የምፈታው እኔ ብቻ ነኝ” ላሉት “ሰራዊታችንስ? የፖሊስ አባላትስ? የእሳት አደጋ ተከላካዮችስ? ሃኪሞቻችን፣ ነርሶቻችን፣መማሕራን፡ ባለነዋዮችን፡ ልጆቻቸው ለዚች አገር መስዋእት የሆኑ እናቶችን ወዴት ሄደው ነው” በማለት ነቅፈዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ሂላሪ ክሊንተን የዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው እጩ ሆነው ተመረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG