ዋሺንግተን ዲሲ —
ለእሥረኞቹ ስንቅና የጤና አገልግሎት እንደማይደርስ ሌሎችም የበረቱ ችግሮችን እየተጋፈጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ቁጥሩ ከሃያ በላይ ሰው ታጉሮበታል ያሉትን የእሥር ሁኔታ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪ ከመቃብር ቤት ጋር አመሣስለውታል፡፡
ሰዎቹ የታሠሩት “በተራ ወንጀል አይደለም” ያለው የሊሙ ወረዳ ፖሊስ የተያዙትም በኮማንድ ፖስት እንደሆነ ገልጿል፡፡
የወረዳው ፖሊስ ኮማንደር ኢንስፔክተር ተሰማ እንግዳ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ሰዎቹ የታሠሩት መንግሥት ያወጣውን ሕግ በመተላለፍ፣ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት፣ ከአዲስ አበባ መሣሪያ በማምጣትና ሌሎችም ሕገወጥ ተግባሮችን በመፈፀም ነው” ብለዋል፡፡
የጤናና የሕግ አገልግሎቶች እንደሚያገኙና ዘመድ እንደሚጠይቃቸው ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡
ሊሙ ሴቃ ወረዳ ውስጥ የታሠሩ ሌሎችም ሰዎች እንዳሉ ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ቢጠቁሙም ኢንስፔክተር ተሰማ ግን “ከተጠቀሱት ሃያ ሰዎች ሌላ የታሠረ ሰው የለም” ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡