በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቢሾፍቱ ወደ 50 የሚጠጉ ተማሪዎች ታሠሩ ተባለ


የተቃውሞ እጆች -በማልታ
የተቃውሞ እጆች -በማልታ

የቢሾፍቱ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ትናንትና እና ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውንና በፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎችና ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

በከተማይቱ የሚገኙ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ሰሞኑን በየትምሕርት ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር የተናገሩት የዐይን እማኞች ከ50 በላይ ተማሪዎች መታሠራቸውን ተናግረዋል።

መረጃውን ለአሜሪካ ድምጽ ያደረሰት አንድ የዐይን እማኝ ስለነበረው ተቃውሞ ሲናገር ፤ ተማሪዎቹ ቀደም ሲል የታሠሩ ተማሪዎቸና መምሕራን እንዲፈቱ የሚጠይቁ ድምፆችን እያሰሙ ተቃውሞ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የቢሾፍቱ ከተማ የፀጥታ ኃላፊ አቶ አቶ አሰቦ በትምሕርት ቤቶቹ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ሰልፍ አለመኖሩን ገልፀው የታሠሩት መስታወት የሠበሩ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ይላሉ፡፡

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ሶራ ሀላኬ ያጠናቀረውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

በቢሾፍቱ ወደ 50 የሚጠጉ ተማሪዎች ታሠሩ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG