ዋሽንግተን ዲሲ —
አራት ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው። ትናንት ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ እንደነበርና ተማሪዎች መታሠራቸውን የዐይን እማኝ መኾኑን የገለፀ ተማሪ ተናግሯል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ቁጥር ከሰላሳ እንደማይበልጥ ይናገራሉ፡፡ በተያያዘም በጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች ሰዎች እየታሠሩ መኾኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ የክልሉ ፖሊስ ምንም የታሠረ ሰው የለም ይላል።
የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ እና ሶራ ሀለኬ ያጠናቀሩትን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።