በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያ ጉዳይ አቤቱታ በአሜሪካ ኮንግረስ ሕንፃ ውስጥ ተሰማ


በዩናትድ ስቴትስ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንዲቆም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:16 0:00

በዩናትድ ስቴትስ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንዲቆም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮምያ ክልል እየታየ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ዛሬ በአሜሪካ ኮንግረስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሕግ መምሪያው ሬይበርን ሕንፃ ውስጥ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙትና ማብራሪያ የሰጡት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል - ዩኤስኤ ዋና ዳይሬክተር አዶቴይ አክዌዪ እስከአሁን ባሉ ግምቶች ኦሮምያ ውስጥ ባለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ምክንያት “ከአራት መቶ በላይ ሰው ተገድሏል፤ በሺሆች የሚቆጠሩ ታስረዋል፤ ቤቶችና የንግድ ሥፍራዎች ወድመዋል” ብለዋል።

ሬይበርን የሕግ መምርያ ቢሮዎች ህንጻ
ሬይበርን የሕግ መምርያ ቢሮዎች ህንጻ

ማብራሪያ ከሰጡት መካከል አንዷ የኦክላንድ ኢንስቲትዩት መሥራችና ዋና ዳይሬክተር አኑራድሃ ሚታል “ኢትዮጵያ ውስጥ እስከአሁን መሬታቸውን በኢንቨስትመንት ስም የተነጠቁ ያሏቸው ከአንድ ሚሊየን ተኩል በላይ ዜጎች ከነባር ይዞታዎቻቸው ላይ ተፈናቅለዋል” ብለዋል።

የአዘጋጆቹን በዩናይትድ ስቴትስ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ዝርዝር ማብራሪያ የተናገረው የኦፕራይድ ዶት ኮም ኤዲተር ሞሐመድ አዴሞ ኦሮምያ ውስጥ ተፈፅመዋል የተባሉትን ጥቃቶችና ጉዳቶች ዝርዝር ተናግሯል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ አባል እንደራሴ ኪት ኤሊሰን ኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ አጋር መሆኗን አመልክተው ኦሮምያ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። ከላይ ያለውን ቪድዮውንም ይመልከቱ።

የኦሮምያ ጉዳይ አቤቱታ በአሜሪካ ኮንግረስ ሕንፃ ውስጥ ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG