በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢንቬስተሮችና የጋዜጠኞች አቤቱታ በአቦቦ ወረዳ ላይ


ጋምቤላ - አቦቦ ወረዳ
ጋምቤላ - አቦቦ ወረዳ

ወደ ጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ሄደው የነበሩ ስምንት ጋዜጠኞች “በመንግሥት ባለሥልጣናት ተደበደብን፣ ተዋከብን፣ ታገትን፣ ያለአግባብ በቁጥጥር ሥር ዋልን” ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል። የወረዳው አስተዳደር አስተባብሏል።

ወደ ጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ሄደው የነበሩ ስምንት ጋዜጠኞች “በመንግሥት ባለሥልጣናት ተደበደብን፣ ተዋከብን፣ ታገትን፣ ያለአግባብ በቁጥጥር ሥር ዋልን” ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል። የወረዳው አስተዳደር አስተባብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ውስጥ “ነዋይ እያፈሰስንና የልማት ሥራ ላይ ተሠማርተን ሳለን ወከባ፣ ሙስናና እንግልት ይደርስብናል” ሲሉ ቁጥራቸው በርከት ያለ ባለሃብቶች ቅሬታቸውን እየገለፁ ናቸው።

ባለሃብቶቹ አቤቱታና በጋዜጠኞች ላይ የደረሰውን ወከባና ጥቃት አስመልክቶ የወረዳው አስተደዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ የጋዜጠኞቹን ክሥ ሙሉ በሙሉ አስተባብለው ከአንድ ባለሃብት ላይ ‘ያለአግባብ ተሰጥቶ ነበር’ ያሉትን የከሰል ምርት ፍቃድ ወረዳው ከማንሣቱ በስተቀር ለባለሃብቶች ጥበቃ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ጋዜጠኞቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ቃላቸውን ተቀብሎና ከወረዳው ባለሥልጣናትም ጋር እየተፃፃፈ መሆኑን የገለፁው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።

ፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዚህ የጋዜጠኞቹ አቤቱታና በሌሎችም ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አሠራርና የሕግ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቪኦኤ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ቀጠሮ ሰጥተዋል።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢንቬስተሮችና የጋዜጠኞች አቤቱታ በአቦቦ ወረዳ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:45:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG