በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቪኦኤ ለጠ/ሚ አብይ የአሜሪካ ቆይታ ሙሉ ሽፋን ሰጥቷል


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሐምሌ / 2010 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ላደረጉት የአምስት ቀናት ጉብኝት የአሜሪካ ድምፅ የተሟላ ሽፋን ሰጥቷል።

ቪኦኤ ለጠ/ሚ አብይ የአሜሪካ ቆይታ ሙሉ ሽፋን ሰጥቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአሜሪካ ድምፅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ሽፋኑን የሰጠው በዓለም ዙሪያ በሚሠራባቸው አርባ አምስት ቋንቋዎች፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን የቀጥታና ተከታታይ ሥርጭቶች፣ እንዲሁም በዌብ ሳይቶቹና በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮቹ ነው።

VOA-LOGO
VOA-LOGO

የአሜሪካ ድምፅ የተለያዩ ዝግጅት ክፍሎች ሪፖርተሮቹንና ቴክኒሻኖቹን አሠማርቶ ከተጓዙባቸው አካባቢዎችና ካደረጓቸው ስብሰባዎች ካስተላለፋቸው ዘገባዎቹ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በዘረጋው የሣተላይት ግንኙነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዋሺንግተን ዲሲ ንግግር በዓለም ዙሪያ ላሉ ተመልካቾች በጥራት እንዲደርስ አድርጓል።

የአሜሪካ ድምፅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከመጀመራቸው ከሣምንታት በፊት በሰጠው በዚህ ተከታታይና የቅርብ ዘገባ በዓለም ዙሪያ ያሉ ተመልካቾችና አድማጮቹ ስለ ኢትዮጵያ የወቅቱ ሁኔታ የቅርብ ክትትል እንዲኖራቸው አድርጓል።

የአሜሪካ ድምፅ በሣምንት ከ230 ሚሊየን በላይ ተመልካችና አድማጭ በዓለም ዙሪያ ያለው እጅግ ግዙፍ የሚድያ ተቋም ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩናይትድ ስቴትስ ቆይታ ላይ እየተዘጋጀ ያለው ዘጋቢ ቪድዮ በቅርቡ ይወጣል። ለናሙና ከዚህ ጋር የተያያዘውን የዘጠና ሰከንዶች የቪድዮ ቅንብር ይመልከቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመስከረም 2011 ዓ.ም አጋማሽ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 73ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝተው የሚያደርጉትን ንግግር ቪኦኤ ሙሉ በሙሉ ያስተላልፋል፤ የቅርብ ዘገባዎችንም ይሰጣል። ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ይቆዩ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG