የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ባለፈው ሣምንት ወደ ጂዳ ሰዑዲ አረቢያ ሄደው የነበረ ጊዜ ንጉሥ ሳልማን ለሁለቱም መሪዎች አድናቆታቸውን ገልፀው ሽልማትም አጥልቀውላቸዋል።
ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያና ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር ያለችበት የሞቀ ግንኙነት ኢትዮጵያን ወደ የመን ጦርነት ይጎትታት ይሆን? የሚል ሥጋት እያሰሙ ያሉ ብዙዎች ሲሆኑ ያንን ሃሣብ በሃሣብ ደረጃ እንደሚያከብሩ ያስታወቁት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ፍፁም አረጋ ሃገሪቱ ወደዚያ ቁርቁስ የምትገባበት ምክንያት እንደሌለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይና በሌሎችም አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ምርምር የሚያደርጉትና ፅሁፎችንም የሚያወጡት ቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በቅርቡ ባወጡት አንድ ፅሁፍ የአካባቢውን ጂዖ ፖለቲካዊ መስተጋብርና ተፅዕኖ አሳዳሪ ያሏቸውን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ፣ ምጣኔኃብታዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ተንትነዋል።
ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ