በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራና የተከፈተው ድንበር


ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ
ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ

ኤርትራ ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን አጋጣሚዎችና ክስተቶች ልትማር ይገባታል የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ የፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አትኩሮት እንዲያገኝ በቅርቡ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ አውጥተዋል።

የኤርትራና የኢትዮጵያ ፀብ፣ ኩርፊያና ቁርሾ እንግዲህ አክትሟል።

ዜጎቻቸው በነፃነት መሸጋገር፣ ተራርቀው የኖሩ ወዳጆች፣ ተጠፋፍተው ወይም ተቆራርጠው የነበሩ ቤተሰቦች እየተገናኙ ናቸው። የሁለቱም ወገኖች ነጋዴዎች እየተሟሟቁ ይመስላሉ። ሃገሮቹም ቢሆኑም ከወደቦች አጠቃቀም አንስቶ ላቅ ባሉ ጉዳዮች ላይ ሊተሣሰሩ ነው።

የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር፤ ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ ግን ሥጋትና ማሳሰቢያ አላቸው።

ኤርትራ የኢትዮጵያን መንገድ ሙሉ በሙሉ ባትቀዳና ባትከተል እንኳ ለዜጎቿና ለሥራ ፈጣሪ ነዋይ አፍሣሾች የተሻሉ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሕዝቧን ነጉዶ ከማለቅ መጠበቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ባለዕውቀትና ባለሃሣብ የውጭ ሰዎችን መሣብ እንደምትችል አመልክተዋል።

ካለበለዚያ አሁን ያለው አዝማሚያና የፍልሰት መጠን “ኤርትራ ባዶዋን ልትቀር ይሆን እንዴ?” የሚል ጥያቄ ማጫሩ እንደማይቀር ተናግረዋል።

በማንኛውም ሃገር ውስጥ ላሉ ሁኔታዎች የመጀመሪያዎቹ ተጠያቂዎች መሪዎች መሆናቸውን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብሩክ ፕሬዚዳንት ኢሣያስም በሃገራቸው ሁኔታና መፃዒ ዕጣ ላይ ጊዜ ሰጥተው ሊያስቡ እንደሚገባ መክረዋል።

ኤርትራ ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን አጋጣሚዎችና ክስተቶች ልትማር ይገባታል የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ የፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አትኩሮት እንዲያገኝ በቅርቡ አውጥተዋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ ቀድሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማትና በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያን በመወከል እስከ ምክትል አምባሳደርነት ባሉ የተለያዩ ደረጃዎች በዲፕሎማትነት አገልግለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም መምህር ነበሩ። ዶ/ር ብሩክ አሁን በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ናቸው። ቀደም ሲል በስክሪፕስ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤትና በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩ ሲሆን የዓለምአቀፍ አመራር ማዕከል /ግሎባል ሊደርሺፕ ሴንተር/ ዳይሬክተርም ሆነው አገልግለዋል። የፉልብራይት ስፔሻሊስት ሆነው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለመሥራት፣ ከኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና ለማጠናከር እንዲሁም የጋዜጠኛነትና ኮምዩኒኬሽንስ ትምህርት ቤቱን ለማገዝ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ቪኦኤ አናግሯቸዋል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ሃሣባቸውን ያግኙ።

ኤርትራና የተከፈተው ድንበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG