በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና አረቢያ ልሣነ-ምድር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን እማኝነት የኢትዮጵያና የኤርትራ የስምምነት ሠነድ ላይ ፊርማቸውን ሲያኖሩ /ፎቶ - ከሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ የተገኘ - ኢንተርኔት - ጂዳ፣ ሳዑዲ አረቢያ፤ መስከረም 2011 ዓ.ም/
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን እማኝነት የኢትዮጵያና የኤርትራ የስምምነት ሠነድ ላይ ፊርማቸውን ሲያኖሩ /ፎቶ - ከሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ የተገኘ - ኢንተርኔት - ጂዳ፣ ሳዑዲ አረቢያ፤ መስከረም 2011 ዓ.ም/

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአረቢያ ልሣነ-ምድር መንግሥታት ጋር ያሉበት የተሟሟቀ ግንኙነት ምናልባት ኢትዮጵያን ወደ የመኑ ጦርነት ይጎትታት ይሆን? የሚል ሥጋት የቀሰቀሰባቸው ጥቂት አይደሉም።

አቶ ፍፁም አረጋ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ፣ ንጉሥ ሳልማን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ከግራ ወደ ቀኝ/ ጂዳ ላይ /ፎቶ - ከሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ የተገኘ - ኢንተርኔት/
ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ፣ ንጉሥ ሳልማን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ከግራ ወደ ቀኝ/ ጂዳ ላይ /ፎቶ - ከሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ የተገኘ - ኢንተርኔት/

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ከሳዑዲ አረቢያው ንጉሥ ሳልማን ሰሞኑን ጂዳ ላይ ሽልማት ተጠልቆላቸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥና የሳዑዲ አረቢያ
አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማንም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ነበሩ። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ልኳል።

ይህ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአረቢያ ልሣነ-ምድር መንግሥታት ጋር ያሉበት የተሟሟቀ ግንኙነት ምናልባት ኢትዮጵያን ወደ የመኑ ጦርነት ይጎትታት ይሆን? የሚል ሥጋት የቀሰቀሰባቸው ጥቂት አይደሉም።

በዚህና በሌሎችም አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ፍፁም አረጋ ከቪኦኤ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገዋል።

ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና አረቢያ ልሣነ-ምድር
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG