በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃሴት ቀን - ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ


ሰሞኑን ላረፉት የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አሸኛኘት እየተደረገ ነው። አስከሬናቸው በብሄራዊው ካቴድራል አርፎ የፀሎትና የዝክር ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

ሰሞኑን ላረፉት የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አሸኛኘት እየተደረገ ነው። አስከሬናቸው በብሄራዊው ካቴድራል አርፎ የፀሎትና የዝክር ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በፀሎትና በሽኝቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአሁኑን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕንና ባለቤታቸውን ሜላኒያ ትረምፕን ጨምሮ በሕይወት ያሉ የቀደሙ ፕሬዚዳንቶች ሁሉ ከነባለቤቶቻቸው ተገኝተዋል።

ከሌሎች ሃገሮችም የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል፤ የዮርዳኖስ ንጉሥ አብዱላ፣ የፖላንድ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ፣ የታላቋ ብሪታንያ ልዑል ቻርልስ ከኀዘንተኛው መካከል ናቸው።

George HW Bush
George HW Bush

ቃለ-ዝክር የሰጡት የመጀመሪያ ልጃቸው አርባ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋከር ቡሽ /ትንሹ/፣ የካናዳ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ብራያን መልሮኒ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ሴናተር አለን ሲምፕሰን እና የትልቁ ቡሽ የራሣቸው የሕይወት ጉዞ መዝጋቢ የሆኑት የታሪክ ሊቅ ጆን ማቼም ናቸው።

ዛሬ ብሄራዊ የኀዘን ቀን ሆኖ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲታሰብና ፌደራል መንግሥቱም ግዝ ሆኖ እንዲውል ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ ያወጡት ሚስተር ትረምፕ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ዕለቱን “የሃሴት ቀን” ብለውታል።

“ይህ የቀብር ሽኝት ሥርዓት አይደለም። ይህ ስለአንድ ታላቅ ሰው፤ ረሀወምና የተከበረን ሕይወት ስለኖረ ሰው ሕይወት ክብር የምናደርስበት የኀሴት ቀን ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ።

/ጆርጅ ዋከር ቡሽ - ዜጋ፣ ወታደር፣ አምባሳደር፣ መልዕክተኛ፣ ዳይሬክተር፣ እንደራሴ፣ ፕሬዚዳንት - ሰኔ 5/1916 ዓ.ም. - ኅዳር 21/2011 ዓ.ም./

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የሃሴት ቀን - ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG