ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የኃይል ሚዛን ተለውጧል። ትናንት በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ ተቃዋሚው ዴሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መምሪያውን የበላይነት ተቆጣጥሯል።
ትውልደ-ሶማሌዪቱ ኢላን ኦማር እና ከኮሎራዶ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለኮንግረስ ሲመረጥ የመጀመሪያ የሆኑት የኤርትራ-አሜሪካዊያን ልጅ ጆዜፍ ንጉሤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ሆነው ተመርጠዋል።
የሜኔሶታዋ የቀድሞ ሶማሊያዊት ስደተኛ ኢላን ኦማርና የሚሺጋኗ ፍልስጥዔም አሜሪካዊት ራሺዳ ጣሊብ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ለመሆን የመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ሴቶች ሆነዋል።
ሪፐብሊካኑ ግን በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ውስጥ የነበራቸውን አብላጫ መቀመጫ አስፍተዋል።
የዚህ ምርጫ ውጤት በአንድ በኩል ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የከበደ ጡጫ ነው ቢባልም በሌላ በኩል ደግሞ አቋማቸውን እንዳጠናከረላቸው ነው የሚነገረው።
ለማንኛውም የዋሺንግተን የፖለቲካ ትንቅንቅ ለመጭዎቹ ሁለት ዓመታት ተባብሶ እንደሚቀጥል ብዙዎች ገምተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፣ አስተያየቶችና ትንታኔ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ