ኒው ዮርክ —
የአፍሪካ ቀንድ “የአፍሪካ ተስፋ እየሆነ ነው” ብለዋል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባ ሦስተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፡፡
ኢትዮጵያ የጀመረችው ለውጥ በሃገር ውስጥም በአካባቢውም አዲስ ተስፋን እየዘራ እንደሆነም አመልክተው ኤርትራ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች ፈጥነው እንዲነሱ ጠይቀዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሥራች አባል የሆነችው ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ቻርተር መጠበቅና ለመርኆቹም መሣካት በየመስኩ እያበረከተች ነች ያሉትን ተግባር ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለዚሁ ጠቅላላ ጉባዔ ያደረጉትን ንግግር ማጣቀሻ ጭምር አንስተው አባል መንግሥታቱን አስታውሰዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ