በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች


የዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ - 2018
የዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ - 2018

ዛሬ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ እየተካሄደ ነው።

አሜሪካዊያን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤታቸው 435 የሕግ መምሪያና ከመቶ መቀመጫዎቹ ሲሦ ያህሉ ለምርጫ ለቀረቡበት የሕግ መወሰኛ ክንፎች እንደራሴዎቻቸውን ለመምረጥ ድምፅ እየሰጡ ናቸው።

በመቶ ሰባ ሺህ የድምፅ መስጫ ማዕከላት እየወጡ ያሉ አሜሪካዊያን በተጨማሪም አገረ ገዥዎችና አቃቢያነ-ሕግም እየመረጡ ናቸው፤ የሕዝብን ውሣኔ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይም ድምፃቸውን እየሰጡ ነው።

በጆርጂያ ግዛት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ለአገረገዥነት፤ በሚኔሶታና በሚሺጋን ግዛቶች ደግሞ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ሴት ተፎካካሪዎች ለተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እየተወዳደሩ ናቸው።

https://projects.voanews.com/muslim-candidates/

በምርጫው ውስጥ ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያንም በስፋት ድምፃቸውን እየሰጡ ሲሆን የተወሰኑት ሃሣቦቻቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አካፍለዋል።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተጠናቀሩ ዘገባዎችና የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ትንታኔ የያዘውን የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ።

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG