ጂማ —
ጂማ ከተማ ላይ ሲካሄድ የነበረው የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ዘጠነኛ ጉባዔ ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር፣ አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
ጉባዔው በተጨማሪም ሃምሣ አምስት የፓርቲውን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሰይሟል።
ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ከተመረጡት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር “ወጣቶች በችግር ጊዜ ድንጋይ መወርወር ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት ሰጥተናቸው ሃገር ማስተዳደር እንደሚችሉ ማስመስከር አለብን” ብለዋል። ኦዴፓ ጉባዔውን ዛሬ አጠናቅቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ቀጥተኛ መገናኛ